ክቡራን የማህበሩ አባላት እና የዘርፉ ባለሙያዎች፣
የኢትዮጵያ ቴክስታይልና አልባሳት ባለሙያዎች ማህበር (ኢቴአባማ) ለሁሉም አባላት እና የዘርፉ ባለሙያዎች በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።
ማህበራችን ሁሉንም አባላት እና የዘርፉን ባለሙያዎች በ2ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ይጋብዛል።
ይህ አመታዊ ጉባኤ የቴክስታይል እና አልባሳት ባለሙያዎች የማህበሩን የእስከ አሁን የስራ አፈጻጸም የሚገመግሙበት፣ በዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ድምጽ የሚሰጡበት እና እርስ በእርስ የሚገናኙበት ወሳኝ መድረክ በመሆኑ የሙያ ማህበሩ አባላት በጉጉት የሚጠብቁት እና የሚሳተፉበት ጉባኤ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
📌 የጉባኤው ዝርዝር መረጃ፦
ስለ ጉባኤው ዝርዝር ፕሮግራም፣ ዕለታዊ አጀንዳዎች፣ እንዲሁም ስለ ስብሰባው ቦታ እና ሰዓት ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከዚህ ኢሜይል ጋር የተያያዘውን ፋይል (Attachment) ይመልከቱ።
📝 የጉባኤው ምዝገባ፦
በጉባኤው ላይ ለመገኘት ቦታዎን ቀድመው እንዲያስከብሩና አስፈላጊውን ዝግጅት እንድናደርግ እባክዎን ከታች ያለውን የጉግል ፎርም ሊንክ በመጫን ምዝገባዎን ያጠናቁ፦
👉 ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ (የGoogle Form ሊንክ)
የእርስዎ መገኘት ለማህበራችን ጥንካሬ እና ለዘርፉ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በጉባኤው ላይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን!
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር፣
የኢትዮጵያ ቴክስታይልና አልባሳት ባለሙያዎች ማህበር (ኢቴአባማ)






