በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት 11ኛው አለም አቀፍ የ‘ጥጥ፣ ቴክስታይል እና የአልባሳት እሴት ሰንሰለት በአፍሪካ ፎረም ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ_ቴክስታይል_እና_የአፓራል_ባለሙያዎች_ማህበር መስረታ ህጋዊ እውቅና ማግኘቱ ተበሰረ።
የኢትዮጵያ_ቴክስታይል_እና_የአፓራል_ባለሙያዎች_ማህበር ሲመሰረት በፕሬዚዳንትነት አንጋፋውን ምሁር ዶ/ር አበራ ከጪ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሲመርጥ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ድ/ር ባዬ ብርሃኑን ከድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ አስመርጧል። አቶ ማርቆስ ወ/ወዳጆን ከኢትዮእጵያ ቴክስታይል ኢንዱስትሪ ልማት ምርምር ማዕከል እና ሰባት የስራ አስፈጻሚን ማስመረጡን በምስረታው ወቅት ተገልጿል።
የማህበሩ አላማ
1ኛ. የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና የአፓራል ሙያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተደግፎ በብቃት እንዲያድግ ማስቻል። ከሁሉም በላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ በመስራት
2ኛ. የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና የአፓራል ኢንዳስትሪ ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ዘርፍ በመሆኑ በሙያ ላይ የተመረኮዘ ጥናትና ምርመር በማካሄድ ዘርፉን ማገዝ
3ኛ. የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና የአፓራል ኢንዱስትሪ ዘርፍ የዓለም አቀፉን ተሞክሮ ለሀገራችን በሚስማማ መልኩ የፖሊሲ ግብዓት በማጥናትና በማዘጋጀት ለፖሊሲ አውጭዎች ማቅረብ
4ኛ. በዘርፉ ያላውን የስልጠና ክፍተት በማጥናትና በማስጠናት የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና የአፓራል አምራች ሰራተኞች ምርታማና ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል
5ኛ. የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና የአፓራል ዘርፉ ያሉን ባለድርሻ አካላትን እርስበርስ የማስትረሳሰር ስራ መስራት
6ኛ. የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና የአፓራል ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአጠቃላይ ውጤታማ ሁኖ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ላይ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ማስቻል እና ሌሎች አላማዎችን የቀፈ ማህበር መሆኑን የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አበራ ከጪ ገልጸዋል።