የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የወርቅ እዮበልዩ በዓል ለማክበር ከመጡ መካከል በቀድሞ የቴክስታይል ቴክኖሎጂ በአሁኑ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምሩቃን የሆኑት አቶ አሸናፊ ታዬ እና አቶ አረዳ ባቱ በህይወት ተሞክሮ ያገኙትን የህይወት ልምድ ለኢንስቲትዩቱ (በሰላም ግቢ) መካከለኛ አመራሮች፣ ለኮርስ ቸሮች እና ከየትምህርት ክፍሉ ለተውጣጡ መምህራን ስለ አእምሮ ውቅር (change of mind set) ስልጠና ሰጡ:: የስልጠናውተሳታፊዎችም ስልጠናውን በሚመለከት በርካታ ሀሳብና ጥያቄዎችን አንስተው ከአሰልጣኞች በቂ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጦበታል::
በኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቴክስታይል ም/ሳይንቲፊክ ዳሬክተር ዶ/ር ሻለሙ ሻረው በስልጠና ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንዳሉት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት የአልማዝ እዮበልዩ በዓሉን በድምቀት ሲያከብር የዩኒቨርሲቲው መስራች የሆነው የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ1955 ዓ.ም በቴክስታይል ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ተመሰረተ:: እሁን ላይ በስድስት የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር ማለትም በቴክስታይል ኢንጂነሪንግ፣ በቴክስታይል ኬሚካል ፕሮሰስ ኢንጂነሪንግ፣ በጋርመንት ኢንጂነሪንግ፣ በሌዘር ኢንጂነሪንግ፣ በፋሽን ዲዛይን እና በቴክስታይልና አፓራል ሜርቻንድዚንግ ትምህርት ክፍሎች እያሰልጠነ የሚገኝ ነው:: እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ በስምንት መርሃ ግብር እና በሦስተኛ ዲግሪ በዘጠኝ መርሃ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ የሚገኝ ተቋም ነው ብለዋል::